የቻይናው አይኤፍኤች ኢንጂነሪንግ በኢትዮጵያ የግንባታ ዘርፍ አሁን ካለበት ደረጃ ከፍ ለማድረግ አላማ ማድረጉን አስታወቀ
በኢትዮጵያ የግንባታ ዘርፍ ፈር ቀዳጅ የሆነዉ አይኤፍኤች ኢንጂነሪንግ ኃላ.የተ.የግ.ማ በሀገሪቱ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዉስጥ ከፍተኛ ተፅዕኖ መፍጠር መቀጠሉን አረጋግጧል።
በኢትዮጵያ እየተጨናነቀ ባለው የግንባታ ኢንዱስትሪ ዉስጥ ትልቅ ለውጥ እና እድገትን የሚያመጣ ቁልፍ ሰው ሆኖ ጎልቶ መዉጣት የቻለዉ ፍቅር አለባቸዉ ይህንኑን ራዕይ ለማስቀጠል ዓላማ ማንገብን አስታውቋል ።
ፍቅር አለባቸዉ በኢትዮጵያ የግንባታ ዘርፉ ዉስጥ በቆየባቸው ዓመታት ለኢንዱስትሪው እድገትና ለዉጥ እንዲያሳይ ማድረግ ከቻሉ ባለሞያዎች መካከል ይገኝበታል።
በቻይና ኮሙዩኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ (ሲሲሲሲሲ) አህት ኩባንያ የሆነው አይኤፍኤች ኢንጂነሪንግ ኃላ.የተ.የግ.ማ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ፍቅር አለባቸው በኢትዮጵያ ያለውን የመሰረተ ልማት ገጽታ ለመለወጥ ከ25 ዓመታት በላይ ጥረት እያደረጉ እንደሚገኝ ይነገራል።
የእሱ ጉዞ የግል ፍላጎትን ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ትስስር በስትራቴጂካዊ የግንባታ ፕሮጀክቶች ለማሳደግ ያለውን ቁርጠኝነት አጉልቶ ማሳየት ተችሏል።
የፍቅር ጉዞ የሚጀምረዉ በምህንድስና ላይ በማተኮር ሲሆን ይህን ተከትሎ በፍጥነት የዘርፉ መሪ ለመሆን እንዲበቃ አስችሎታል ። አይኤፍኤች ኢንጂነሪንግ ሲቀላቀሉ የአዲስ አበባ ቀለበት መንገድ ፕሮጀክትን ከአንድ እስከ ሶስት ባለው ደረጃ በማጠናቀቅ ትልቅ ሚና መጫዉቱን ይገለጻል።
ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በከተማው ውስጥ ያለውን የትራንስፖርት አገልግሎት ማሻሻል ብቻ ሳይሆን ለወደፊት ልማት መሰረት ጥሏል። በእርሳቸው መሪነት አይኤፍኤች ኢንጂነሪንግ በአዲስ አበባ ብቻ ከ50 በላይ ፕሮጀክቶችን በድምሩ ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ በማጠናቀቅ በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል።
አይኤፍኤች ኢንጂነሪንግ በኢትዮጵያ የሚያከናዉናቸዉ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች በተጨማሪ የማህበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ፍቅር አለባቸዉ ተቋሙ የማህበራዊ ኃላፊነቱን እንዴት እየተወጣ እንደሚገኝ ሲያብራሩ “በፕሮጀክታችን እቅድ ዉስጥ ሆነዉ የምንሰራቸው መንገዶች የተለያዩ ማህበረሰቦችን ያገናኛሉ” የሚሉት ፍቅር ከዚህ በተጨማሪ “በአንደኛው ፕሮጀክት ለአካባቢው ነዋሪዎች ነፃ የመንገድ ተደራሽነት አቅርበናል፣በሌሎቹ ደግሞ ለትምህርት ቤቶች ውሃ አቅርበናል፣አምቡላንስ ለጤና ጣቢያ ሰጥተናል።” ሲሉም አስረድተዋል ።
ኩባንያው ከከተማ አስተዳደሮች ጋር በቅርበት እንደሚሰራ እና አስፈላጊ ቁሳቁሶችን እንደ አሸዋ እና ሲሚንቶ በማቅረብ ለተቸገሩት ቤቶችን ለመገንባት የተለያዩ እርዳታዎችን እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ከየትኛውም ግንባታ ከሚገኝዉ ከጥቅም ባለፈ እንደ ተቋም የማህበራዊ ሃላፊነት በመወጣት እንደሚገባ የፍቅር እምነት ሆነዉ ቆይቷል።
ኩባንያው ከታላቁ ሩጫ ጋር ላለፉት ሁለት አስርት የማይረሳ ግንኙነት መፍጠር እንደቻለ ይነገራል ። ይህ የረዥም ጊዜ ግንኙነት የመንገድ ደህንነትን እና የህብረተሰቡን ተሳትፎ በሩጫ ዝግጅቶች በማስተዋወቅ አጋርነቱን እያሳየ ይገኛል ።
“የእኛ ሃላፊነት በታላቁ ሩጫ የሚካሄዱ ዝግጅቶችን ስፖንሰር ማድረግ ነው” ውድድሩ የሚካሄደው በ አይኤፍኤች ኢንጂነሪንግ በተገነቡ መንገዶች ላይ ሲሆን ይህም አስተማማኝ የትራንስፖርት አውታር ለመፍጠር ያላቸውን ቁርጠኝነት ያጠናክራል ሲል ፍቅር ተናግሯል።
ከ45 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የወሮታ – ወልዲያ መንገድ ሲሰራ ከልጅነቱ ጀምሮ የመመልከት ዕድል አጋጥሞታል። ይህ ቀደም ብሎ ለመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች መጋለጥ ለምህንድስና ያለውን ፍቅር በማቀጣጠል አሁን ባለበት ጎዳና ላይ እንዲጓዝ አድርጎታል።
ከቻይና ኩባንያዎች ማለትም ከሲሲሲሲ ጋር የመሥራት ልምድ ለእሳቸውም ሆነ ለኢትዮጵያ የግንባታ ዘርፍ ለውጥ ማምጣቱን ይናገራሉ ። ከቻይና ኩባንያዎች ጋር አብሮ መሥራት የአንድ ትልቅ ቤተሰብ አካል ከመሆን ጋር ተመሳሳይ መሆኑን ገልጸዋል።
“የስራ አካባቢው የትብብር ነው፤ ለሥራው ባላችሁ ተነሳሽነት ሙሉ በሙሉ እንድትሳተፉ ይበረታታሉ” ሲል የረዥም ጊዜ የስራ ልምድን ወደ ቤተሰባዊነት መተሳሰብ መቀየር መቻሉን ያስረዳል። ይሁን እንጂ በተለይም አንዳንድ ጊዜ አካባቢን በማስተዳደር ላይ ችግሮች የሚስተዋሉ ሲሆን አብዛኛዎቹ አስተዳዳሪዎች ቻይናውያን ናቸው እና አለመግባባቶች አሉ።
እነዚህ መሰናክሎች ቢኖሩም፣ ፍቅር በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ውስጥ ትብብርን በከፍተኛ ደረጃ ማሻሻል ተችሏል ብሎ ያምናል። የአቅም ግንባታ እና ሙያዊ እድገት ፍቅር በሥራው ላይ ሲያሰላስል እንደ ሲሲሲሲ ያሉ የቻይና ኩባንያዎች መቋቋሙ የአገር ውስጥ ኮንትራክተሮችን አቅም ከፍ እንዳደረገው ይጠቅሳል።
“ከእነዚህ ድርጅቶች ጋር አብሮ በመስራት ብዙ ተምረናል” ብሏል። “በጋራ እውቀትና ልምድ ዛሬ ብዙ ኮንትራክተሮች አዲስ ከፍታ ላይ ደርሰዋል ሲልም አክሏል።
አይኤፍኤች ኢንጂነሪንግ ሙያዊ እውቀትን ለሀገር ውስጥ ሰራተኞች በማስተላለፍ ለተሳካ የፕሮጀክት አፈፃፀም አስፈላጊ የሆኑ ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ በመርዳት ትልቅ ሚና መጫወት ችሏል። ይህ የአቅም ግንባታ አካሄድ በኢትዮጵያ የግንባታ ዘርፍ እድገትን ለማስቀጠል ወሳኝ መሆኑን ፍቅር አስረግጦ ተናግሯል።
አይኤፍኤች ኢንጂነሪንግ የሁለት አስርት ዓመታት በዘርፉ ላይ ማሳደር የቻለዉን በጎ ተፅእኖን በማስታወስ የተመሰረተበትን 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በኢትዮጵያ እያከበረ ይገኛል ።
ይህም ኩባንያው በመላ ሀገሪቱ መሰረተ ልማቶችን በማሻሻል ያስመዘገበውን ውጤት አጉልቶ ያሳያል። ድርጅቱ በአዲስ አበባ ቀለበት መንገድ እና በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የተለያዩ የመንገድ ማሻሻያ ግንባታዎችን ጨምሮ በተለያዩ ከፍተኛ ፕሮጄክቶች ላይ መሳተፉን ፍቅር ገልጿል ።
የኩባንያውን የሁለት አስርት ዓመታት አገልግሎትን ለማስታወስ የ2022 የ አይኤፍኤች የዱላ ቅብብል ዉድድርን ስፖንሰር አድርጓል ።
እነዚህ ውድድሮች በተሳታፊዎች መካከል የቡድን ግንባታን ከማበረታታት ባለፈ ስለ መንገድ ደህንነት ግንዛቤን የሚያሳድጉ መቶናቸዉ ተገልጿል።
በግንባታው ዘርፍ ላይ ያሉ ተግዳሮቶች ከፍተኛ መሻሻል ቢታይም በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ አሁንም ፈተናዎች እየተነገረ ይገኛል።
ከእነዚህ መካከል የቁሳቁስ፣የቁጥጥር መሰናክሎች እና የውጪ ኮንትራክተሮች ፉክክር ዋጋ መጨመር በአገር ውስጥ ንግዶች ላይ ቀጣይነት ያለው ስጋት ፈጥሯል።
እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የመንግስት አካላት እና የግል ባለድርሻ አካላት ትብብር እንደሚያስፈልግ አቶ ፍቅሬ አፅንኦት ሰጥተዋል።
“መንግስት ለሀገር ውስጥ ኮንትራክተሮች እድገት ምቹ ሁኔታ መፍጠር አለበት” ይላል። ፖሊሲዎች እድገታችንን ከማደናቀፍ ይልቅ የሚደግፉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በጋራ መስራት አለብን ሲሉ ተደምጠዋል ።
የወደፊት ራዕይ ወደ ፊት ስንመለከት ፍቅር አፋጣኝ የመሠረተ ልማት ፍላጎቶችን የሚያሟላ ብቻ ሳይሆን የረዥም ጊዜ የኢኮኖሚ መረጋጋትን የሚያጎናጽፍ የኮንስትራክሽን ዘርፍን ይሳያል።
የማህበረሰብ ደህንነትን በማጎልበት ለአካባቢ ጥበቃ ቅድሚያ ለሚሰጡ ዘላቂ ልምዶች መጎልበት እንዳለበት ይሟገታል። መንገድን ብቻ ሳይሆን ግንኙነቶችን በመገንባት ላይ ማተኮር አለብን ሲል አስረግጦ ተናግሯል።
“ሁሉም ባለድርሻ አካላት ማለትም የመንግስት ኤጀንሲዎች፣ የግል ኩባንያዎች እና ማህበረሰቦች ትብብርን በማጎልበት ለኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋ መፍጠር እንችላለን” ያሉት አቶ ፍቅር አለባቸው በኢትዮጵያ የግንባታ መልክዓ ምድር ያካሄደው ጉዞ ለሙያዊ ልህቀት እና ለማህበራዊ ኃላፊነት ያለዉን አበርክቶ በግልጽ ማሳየት ችሏል ።
የአይኤፍኤች ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆን በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ማህበረሰቦችን በሚጠቅሙ ስልታዊ ፕሮጀክቶች አወንታዊ ለውጥ ማምጣታቸውን አሁንም ቀጥሏል።
ለአቅም ግንባታ፣ ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር እና በማህበረሰብ ተሳትፎ ላይ ያለው ቁርጠኝነት የኢትዮጵያን የመሰረተ ልማት ግንባታ እጣ ፈንታ በመቅረጽ ረገድ ቁልፍ ሚና እንዲጫወት አድርጎታል።
በዘርፉ ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶች ቢቀጥሉም ፍቅር በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ውስጥ በሚሳተፉ ሁሉም ባለድርሻ አካላት መካከል በጋራ በሚደረገው ጥረት እድገት እና ፈጠራ ላይ ስላለው እምቅ አቅም ተስፋ እንዳለው ተናግሯል ።

